Topic: The Insider Threat – Human Capital Deficit
The emerging financial landscape is currently grappling with a critical structural crisis. A recent analysis reveals a staggering 66.7% deficit in IT human capital within newly established financial institutions. This shortage is more than an operational bottleneck; it is a primary catalyst for systemic vulnerability. Consequently, these institutions have recorded a collective loss of 1.3 Billion ETB due to systemic fraud.
The correlation is clear: the human capital gap directly empowers "social engineering" tactics. When IT departments are understaffed and professionals are overstretched, internal controls weaken and rigorous monitoring becomes impossible. This environment allows malicious actors to exploit psychological manipulation and procedural lapses. The "Insider Threat" thrives in this vacuum, as employees lack the continuous training and technical oversight necessary to detect sophisticated deception. To stem the
1.3 Billion ETB drain, financial institutions must prioritize closing the 66.7% staffing gap, recognizing that robust cybersecurity is built on human expertise rather than software alone.
ርዕስ፦ የውስጥ ስጋት – የሰው ኃይል እጥረት
በኢትዮጵያ በማደግ ላይ ያሉ የፋይናንስ ተቋማት በአሁኑ ወቅት ከባድ የሆነ መዋቅራዊ ቀውስ ውስጥ ይገኛሉ። የቅርብ ጊዜ ጥናቶች እንደሚያሳዩት በእነዚህ ተቋማት ውስጥ የ66.7% የአይቲ (IT) ባለሙያዎች እጥረት ይስተዋላል። ይህ ከፍተኛ የክህሎት ክፍተት ከሥራ መደራረብ ባለፈ ለተቋማቱ ደህንነት ዋነኛ ስጋት ሆኗል። በዚህም ምክንያት ተቋማቱ በድምሩ ከ 1.3 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመት የሥርዓታዊ ማጭበርበር ኪሳራ ደርሶባቸዋል።
በባለሙያ እጥረት እና በደረሰው ኪሳራ መካከል ያለው ግንኙነት ቀጥተኛ ነው። የሰው ኃይል ክፍተቱ "ሶሻል ኢንጂነሪንግ" (ሰዎችን በማታለል መረጃ የመውሰድ ዘዴ) ለሚባለው የማጭበርበር ዘዴ በር ከፍቷል። የአይቲ ክፍሎች በበቂ ባለሙያ ካልተደራጁ፣ የውስጥ ቁጥጥር ሥርዓቱ ይላላል፤ ጥብቅ ክትትል ማድረግም የማይቻል ይሆናል። ይህ "የውስጥ ስጋት" (Insider Threat) የሚመነጨው ሠራተኞች የማታለል ሙከራዎችን ለመለየት የሚያስችል ቀጣይነት ያለው ስልጠና እና የቴክኒክ ድጋፍ በማያገኙበት ሁኔታ ነው። ስለዚህ፣ ይህንን
1.3 ቢሊዮን ብር የሚጠጋ ኪሳራ ለመቀነስ የ66.7 በመቶውን የባለሙያ ክፍተት መሙላት እና በሰው ኃይል ልማት ላይ መዋዕለ ንዋይ ማፍሰስ ለዘርፉ ደህንነት ወሳኝ መፍትሔ ነው።